ቃና ዘገሊላ - ዲ/ን አሸናፊ መኮንን
ቃና ዘገሊላ - ዲ/ን አሸናፊ መኮንን
$25.00
ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከመሰረቱ ሳይሆን ከጉልላቱ መሥራት ጀመረ ይላል ። ምድራዊ ባለሙያ መጀመሪያ መሰረቱን ይደለድላል ፣ ከዚያ ወደ ጉልላቱ ይሄዳል ። እግዚአብሔር ግን ከሰማያት ጀምሮ ምድርን ይመሰርታል ። እግዚአብሔር ከመጨረሻው መጀመር ይችላል ። በቃና ዘገሊላ የሆነውም ይህ ነው ። ባለቀ ነገር ላይ ለዘመናት የሚተረክ ተአምር ሰራ ። ጌታችን ለራሱ አንድ ቀን እንኳ አልኖረም ። ሠላሳ አመት ቅድስት እናቱን ሲያገለግ ነበረ ፣ ከሰላሳ አመት በኋል ሰማያዊ አባቱን ሊያገለግል ወጣ ። ከሦስት ቀን በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ ተርቦ ነበረ ። ረኃቡን ለማስታገስ ግን ታምራት አላደረገም ። አሁን ግን የሰዎችን ጉድለት አምላካዊ ኃይሉን ይጠቀማል ። እርሱ በዘመኑ ሁሉ አንድ ቀን ለራሱ አልኖረም ። ዛሬ ለራሴ አልኖርኩም የሚሉ ብዙ እሮሮዎች ይሰማሉ ። ለራሳቸው በእውነት ያልኖሩ ሰዎች ክርስቶስን መስለውታል ።
Quantity:


![Screenshot_20170427-224618[4102].jpg](https://images.squarespace-cdn.com/content/v1/549254f9e4b0272178855f29/1493359858668-BVCNQF8S5CIYTW30YSNX/Screenshot_20170427-224618%5B4102%5D.jpg)