እስካሁን የሰራናቸውና በመሰራት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በጥቂቱ:
እስካሁን የሰራናቸውና በመሰራት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በጥቂቱ:
ብሉያትንና ሐዲስ ኪዳንን ያካተተው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሐይማኖት ዘመነ ፕትርክና ወቅት የታተመው ፹፩ አሀዱ አትም ለጥናትና ለማጣቀሻነት ይሆን ዘንድ በቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝና ፈቃድ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስተባባሪነትና በአለም የመጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር በኩል ታተመ ።"ድንበር የለሽ ፀጋና ተስፋ" አብሮ ከሕዝብ ግንኙነቱ ጋር እየሰራን ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ እያሰራጨን ነው።
ለወንጌል ስርጭትና በዓለም ላይ እየተዘዋወሩ እንዲሰብኩ የአሜሪካዊ ዜግነት ፓስፓርት እንዲኖራቸው ለ 1 አገልጋይ ፕሮሰሱንና ክፍያውን አድርገናል ።
በደብረ አሚን ጎንደር ለአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚሆን ሕንፃ አንድ ክፍል በሐላፊነት ወስደን በማስገንባት ላይ ነን ።
ለኦርቶዶክሳዊ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት የስድስት ወር ወጪ ኢትዮጵያ ወስጥ ሸፍነናል ።
በኢትዮጽያ ለሚገኙ 18 ልጆች ለትምህርታቸው የሚያስፈልጋቸውን ማገዝና ለተራቡት የምግብ ወጭ መሸፈን ላይ ነን።
ከኢትዮጽያ በቅርብ ለመጡ 2 ተማሪዎች የአጭር ግዜ ኮርስ ወጭ ሸፍነናል።
ለወንጌል አገልግሎት የሚውል ካሜራዎችና የተለያዩ ቁሳቁሶች ለቤተክርስትያንና አገልጋዮች አበርክተናል::
የእንግሊዘኛ ወንጌል ትምህርትና ሥርዓተ ቅዳሴ በግእዝ ዜማ በቤተክርስትያን እንዲከናወን የአገልጋዮች ወጪ ሸፍነን ጉባዔውን አቀናብረናል::
አለም አቀፍ የኦርቶዶክስ ወንጌል ስርጭት በዩቱብ 〉970 ቪዲዮ፣ 〉7700 ሰብስክራይበር:ጠቅላላ እይታ 〉3 ሚሊየን በላይ