google2b57bc78837a8270.html

ቃና ዘገሊላ - ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

kf.jpg
Screenshot_20170427-224618[4102].jpg
kf.jpg
Screenshot_20170427-224618[4102].jpg

ቃና ዘገሊላ - ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

$25.00

ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከመሰረቱ ሳይሆን ከጉልላቱ መሥራት ጀመረ ይላል ። ምድራዊ ባለሙያ መጀመሪያ መሰረቱን ይደለድላል ፣ ከዚያ ወደ ጉልላቱ ይሄዳል ። እግዚአብሔር ግን ከሰማያት ጀምሮ ምድርን ይመሰርታል ። እግዚአብሔር ከመጨረሻው መጀመር ይችላል ። በቃና ዘገሊላ የሆነውም ይህ ነው ። ባለቀ ነገር ላይ ለዘመናት የሚተረክ ተአምር ሰራ ። ጌታችን ለራሱ አንድ ቀን እንኳ አልኖረም ። ሠላሳ አመት ቅድስት እናቱን ሲያገለግ ነበረ ፣ ከሰላሳ አመት በኋል ሰማያዊ አባቱን ሊያገለግል ወጣ ። ከሦስት ቀን በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ ተርቦ ነበረ ። ረኃቡን ለማስታገስ ግን ታምራት አላደረገም ። አሁን ግን የሰዎችን ጉድለት አምላካዊ ኃይሉን ይጠቀማል ። እርሱ በዘመኑ ሁሉ አንድ ቀን  ለራሱ አልኖረም ። ዛሬ ለራሴ አልኖርኩም የሚሉ ብዙ እሮሮዎች ይሰማሉ ። ለራሳቸው በእውነት ያልኖሩ ሰዎች ክርስቶስን መስለውታል ።

 

Quantity:
ADD TO CART