የኑሮ መድኀን - በዲያቆን አሸናፊ መኮንን

CropperCapture[134].jpg
CropperCapture[134].jpg
sale

የኑሮ መድኀን - በዲያቆን አሸናፊ መኮንን

12.00 15.00

የመጀሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጠል ሰንገልጥ በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ሃያ ሰድስት ቁጥሮች እነደተጓዝን የምናገኘው ቃል አለ ። ይህ ቃል የሰውን ክብር ከሚገልጡ ቃሎች የመጀመሪያውም የዳርቻውም ነው ። ሰውን በሚመለከት  የመጀመሪያው መለኮታዊ ቃለ ጉባዔ ሊሆን ይችላል ። " እግዚአብሄርም አለ: ~ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር ፣ " (ዘፍ• 1÷26)  ። ሰውን በሚመለከት የመጀመሪያው የሥላሴ ምክር ነው ። ሰው በስህተት ወይም በአጋጣሚ የተፈጠረ ሳይሆን መለኮታዊ አጀንዳ የተያዘበት ፍጡር ነው ። እያንዳንዳችን የራሳችንና የወላጆቻችን እቅድ ሳንሆን የእግዚአብሔር ዕቅድ ነን ። " ሕገ ወጥ ወላጆች ሊኖሩ ቢችሉ እንኳ ሕገ ወጥ ልጆች ግን የሉም ። " እስቲ እኔ አጋጣሚ አይደለሁም ÷ እኔ የእግዚአብሔር ዕቅድ ውጤት ነኝ ። ÷ መነሻዬ እግዚአብሔር ነው " ብለን ለራሳችን እንናገር ።

Quantity:
Add To Cart