ጥቂት ዕረፉ - በዲያቆን አሸናፊ መኮንን

CropperCapture[199].jpg
CropperCapture[199].jpg
sale

ጥቂት ዕረፉ - በዲያቆን አሸናፊ መኮንን

10.00 15.00

ሰዎች የበላይነት ስሜት የሚሰማቸው ከሆነ የበታችነት ስቃይ በውስጣቸው አለ ማለት ነው ። የሆነውን የተቀበለና በሆነው እግዚአብሔርን የሚያመሰግን ከዚህ ስቃይ የዳነ ነው ። ስለ ራስ አብዝቶ መናገር ፣ እኔ የሚል ቃል ማብዛት ሌሎችን በንቀት መመልከት ……የበታችነት ስቃይ የሚወልደው ነው ።የበላይነት ስሜት መሰረቱ የበታችነት ስሜት ነው ።በዓለም ላይ የተነሡ ብዙ አምባ ገነን ነገሥታት በአስተዳደጋቸው ብዙ ንቀት ያስተናገዱ እንደ ነበሩ ታሪካቸው ያስረዳል ። የበታችነት ስሜት የሚወለደው ሁለተኛው ችግር ሐሜተኛነት ነው ። ሐሜት ሰውየውን ማንቋሸሽ ስለ እርሱ ወይም እርሷ አሳንሶ መናገር ነው ። የበታችነት የሚሰማቸው ሰዎች የበላያቸው የመሰላቸውን ሰው ዝቅ አድርገው ማማት ከራሳቸው ጋር የሚያስተካክላቸው ስለሚመስላቸው እፎይታ ያገኛሉ ።

Quantity:
Add To Cart